Would you like to notify someone you've mentioned them?
More
About
Memories
Give
Obituary
Events
Photo
Story
Condolence
Video
My deepest condolences to her family and friends! Her life is well lived, and she needs to rest in peace! Let go Muluberhan, let go Colonel; Let go.....
ሰማይ ተከፈተ
ሰማይ ተከፈተ ማሕሌት ተሰማ
ዝማሬ መላእክት ያለው ልዩ ዜማ
ከሱራፌል መሐል አብራ ተቀላቅላ
አንድ ድምፅ አብራ አለች ያላት ልዩ ቃና
ከምትወደው አምላክ ከፊቱ የቆመች
በጣም የምንወዳት በጣም የምትወደን ዛሬ አንድ ነፍስ አለች
በነጩ ዙፋን ፊት በደስታ የቆመች
በምትወደው ዜማ እያሸበሸበች
ከእርሱ ፊት የቆመች ይቺ ነፍስ የማነች
በምድራዊ ሕይወት ምን አይነት ነበረች
ምን አረጋ ምን ሠርታ ለዚህ ክብር በቃች
ከፀዳለ ማርያም የሕይወት ማሕደር
ከሠራችው ሁሉ ጥቂት ሲመረመር
ጎልቶ የሚወጣው ያበቃት ለክብር
ምስጋናና፤ ዕምነት፤ ጽናትና ፍቅር
አነዚህን አይተናል ቆማ ስትመሰክር
እምነቷ ልዩ ነው ወደርም የሌለው
ከቅዱሳን ተራ ነው ሚደመረው
ፅናቷም እንዲሁ ምንም አቻ የለው
እንደወርቅ በእሳት ነው ተፈትኖ ያለፈው
የጻድቃን ሰማዕታት ታሪክ ሲነገረን
ተረት ተረት እንጂ እውነት የማይመስለን
ይኸው እንድናምን አምላክ እርሷን ሰጠን
አይተናል ቀን በቀን ስትኖር ይህንን
ሰለስቱ ደቂቅ እንዳመሰገኑ በእሳት ውስጥ ሆነው
የማሕሌት ምስጋና ከቶ የማያልቅ ነው
የዝማሬው ቃና ከአፏ የሚፈሰው
ከነዳዊት ጎራ የሚደምራት ነው
ከሁሉም የሚበልጥ የማሕሌት ነገር
አብልጦ የሰጣት ወርቅ የሆነ ፍቅር
ብዙ ብዙ ፍቅር
ከማዕረጋተ ነፍስ ከቁንጮው ላይ ያለው
አምላክን ፊት ለፊት ለማየት የሚያበቃው
ትልቁ ችሎታ መውድ ነው ፍቅር ነው
ሃጥኡን ፃድቁን እኩል የወደደ
አምላክን ለማየት እርሱ ነው የታደለ
ከማሕሌት መለየት በጣም የሚከብደው
እያንዳንዳችንን ስለመትወደን ነው
ተቀድቶ የማልቅ ከእርሷ የሚፈሰው
ለትሽ ትልቁ ፍቅሯ እኩል ነው
ታዲያ ለዚች ነፍስ ምን እናድርግላት
እኔ እንደሚመስለኝ የሠጠችን ፍቅር መልሰን ብንሰጣት
በፀሎት በዜማ በክብር ብንሸኛት
ከዚህ አለም አሻግሮ አምላክ ፊት ያቁማት
ከቅዱሳን ጋራ አብሮ ይደምራት
ምን እንደምል ግራ ገብቶኛል
ማሒ የዘመናችን ድንቅ ጀግና ወጣት እንደነበረች
ከአንደበቷ ለመረዳት ብዙም አላዳገተኝም
በመጨረሻው ሰአት ያስተላለፈችው መልእክት በእውነቱ የሚደንቅ ነው እንዲህ አይነት ጥንካሬ እና ልበሙሉነት ሰው አለው ብዬ አልገምትም ነበር በእውነት ጀግና እና አስተማሪ ወጣት ነው ያጣነው
ነፍስ ይማር
የታባቱ ሞትም ይሙት!!
° ° ° °
እባካችሁ ዘመዶቼ -
ስሞት ሞትም አብሮኝ ይሙት፣
በሳቅ በደስታ ግደሉት፣
በሃሴት በዕልልታ ውገሩት፣
እባካችሁ ዘመዶቼ-
ለሞት የልብ ልብ አትስጡት፣
ናቁት አጥላሉት አውግዙት፣
በሙሾ ግነን አትበሉት፣
በሞቴ፣ እንዳታስደስቱት።
እንደ ዶርዜ ወንድሞቼ፣
በሳቅ ታጅቤ ኮርቼ፣
ሞቴን በዘፈን ሞልቼ፣
በዳንኪራ ሰበቃና፣ በዘፈን ሆይታ አካትቼ፣
በሠርጌ ብቀበር ሞቼ፣
እፀድቅ ነበር ባትረሱ፣
በእንባ ውሌን ባታፈርሱ።
በሳቅ ጉዞ ፍታት ፍቱኝ፣
በሙሾ ዋይታ አታጅሉኝ፤
እናቴም ፊትሽ አይክሰል፣
በእልልታ ብርሃን ይንበልበል፤
በእረፍቴ እንዳታፌዥብኝ፣
በሠርጌ እንዳታለቅሽብኝ።
ገጽሽ በጭንቅ አይወረስ፣
ልብሽ በኅዘን አይላበስ፣
በሆድሽ ሞት አይፀነስ፣
ዕንባ በአይንሽ አይቋጠር፣
የሞት ቅስሙ እንዲሰበር።
አዎን፣ አደራ፣ አደራችሁ፣
የሙት ውሌን ተቀበሉኝ፣
ደስታዬን ተካፈሉኝ፣
ለንስሃ ሞት አይደለም-
ለፍሠሐ እረፍት አብቁኝ፣
ለፍሠሐ እረፍት አብቁኝ፤
በዶርዜ እስክስታ አስቀብሩኝ፣
በእልልታው ጉዞ አሳጅቡኝ፣
በጦሩ ችቦ አሳጥሩኝ፣
ጭብጨባችሁ በስልቱ ይውረድ፣
ዛፍ ቅጠሉም አብሮ እስኪረግድ፣
ሀገር ምድሩም ያቅራራ፣
ሀሴት ነው ይበል፣ ጆቢራ፣
ሠርጌ ነው፣ ይምታ ዳንኪራ፣
እንዲህ ስሜት ሲፍለቀለቅ-
ሲፈነድቅ ሲግል ሃሞት፣
ቱማታው ሲዋጥ በላቦት፣
ሆይታ በሆይታ ሲራኮት፣
ማሳለፊያ መግቢያ ሲያጣ፣
ፍርሃት ገበናው ሲራቆት መቃረቢያ ፍንጭ ሲያጣ፣
በእልልታ ሲወገር ብሶት፣
ብቻ ነው፣ ሞት እራሱ የሚሞት።
ሞትም አብሮኝ ይሙት!
በእልልታችሁ ግደሉት፣
በዳንኪራችሁ ዉገሩት፣
ከአጥንቴ በታች ቅበሩት።
ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን፤ ዶርዜ ሰፈር – 1963 ዓ.ም.
You have template text that hasn't been filled in yet.
Do you want Ever Loved to notify subscribers of these changes?
Get notified when new information is shared or changed on this website.